Skip to main content

በከተማችን በአላሙራ ተራራ አከባቢ በታቦር ክ/ከተማ በፋራና ሂጣታ ቀበሌዎች ያለውን የውሃ እጥረት ለመቅረፍ ትልቁ የረጅም ጊዜ ፕሮጀክት እስኪጠናቀቅ የአጭር ጊዜ መፍትሄ የሚሆን ሥራ የሀዋሳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ ድርጅት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ መድቦ ሥራ ጀምሯል::

ይህ ሥራ ቀደም ሲል ተጀምሮ የውሃ መስመሩ የሚያልፍባቸው መስመሮች በግንባታ ተዘግቶ የነበረውን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና የከተማችን ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ተረባርበው መስመሩ እንዲከፈት በማድረጋቸው ከልብ እናመሰግናለን በሚል መልዕክት የድርጅቱ ዋና ስራስክያጅ አቶ ዳዊት አስተላልፈዋል ።

Image
y